ለ 5 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው ዕለት በዕጣ ሊሰጡ ነው

አዲስ አባባ፣ ሰኔ፣ 22፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) አነስተኛ ገቢ ላላቸው 5 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው ዕለት በዕጣ እንደሚተላለፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስታዳደር አስታወቀ።

የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ይህ ዕጣ በነገው ዕለት በጌትፋም ሆቴል እንደሚወጣ ኪንቲባ ድሪባ ኩማ ተናግረዋል።

በነገው ዕለት በዕጣ የሚተላለፉት የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የከተማ አስተዳደሩ በ400 ሚሊየን ብር ከቤቶች ልማት ኤጀንሲ የገዛቸው እንደሆኑ ታውቋል።

በጋራ መኖሪያ ቤት እጣው ወርሃዊ ደመወዛቸው እስከ 3 ሺህ 500 የሆነና አምስት ዓመት የሚደርስ አገልግሎት ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

እነዚህ በዕጣ ለሚተላፉ ቤቶች በወር እስከ 315 ድረስ ተመን እንዳወጣላቸው አስተዳደሩ አስታውቋል።

በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከማዋን ነዋሪዎች የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።

ምንጭ፥ ፋና

የእጣው አሸናፊዎች ስም ዝርዝር እንደተገኘ አዲስኒውስ በዚሁ ድረገጽ ላይ ስለምናወጣ የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ በማድረግ ይከታተሉን።

AddisNews is not responsible for the contents or reliability of any other websites to which we get contents from and provide a link and do not necessarily endorse the views expressed by them.

Article first published here

Recommended For You

About the Author: EthioForum