በሰሜን ተራሮች ፓርክ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እስራኤላውያን ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ገቡ

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተቀሰቀሰውን ሰደድ እሳት የማጥፋት ስራን የሚያግዝ የእስራኤል የባለሙያዎች ቡድን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል። ከደቂቃዎች በፊት በደረሰኝ መረጃ መሰረት ቡድኑ አሁን ጎንደር ገብቷል። በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ እንደተናገሩት እስራኤል የኢትዮጵያ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው የባለሙያዎች ቡድኑን የላከቸው።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ባለፈው አርብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከእስራኤል አቻቸቸው ብኒያሚን ንታኒያ ጋር በእስራኤል ድጋፍ ዙሪያ በስልክ መወያየታቸውንም ነው ያለከቱት።

10 አባላት ያሉት ይህ የባለሙያዎች ቡድን ከእስራኤል የእሳት አደጋ ብርጌድ የተውጣጣ ሲሆን፥ በሰደድ እሳት ከፍተኛ እውቀት እና ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች መሆናቸውን ምክትል አምባሳደሩ አስታውቀዋል። ቡድኑ ወደ ደባርቅ ያመራ ያመራ ሲሆን፥ የሰደድ እሳቱ ወዳለበት ሰፍራ በማቅናት እሳቱን የመቆጣጠር ጥረትን ያግዛሉ ብለዋል።

Via FBC

AddisNews is not responsible for the contents or reliability of any other websites to which we get contents from and provide a link and do not necessarily endorse the views expressed by them.

Article first published here

Recommended For You

About the Author: EthioForum